ለስራ ፈጣሪዎች የሚሰጥ የዘመናዊ ቢዝነስ መርሆዎች አጭር ስልጠና(በኢንተርኔት)

ስልጠና አሰጣጥ አይነት፡ ቪድዮ ስልጠና በቴሌግራም

ቋንቋ፡ አማርኛ

የስለጠናው ተጠቃሚ፡ ነባር አምራች ሆነው ስራቸውን ለማዘመንና ለማሳደግ የሚሹ እና አዲስ ምርት ስራ ለመመስረት ላቀዱ ጀማሪ አምራቾች

ስለጠናው አዘጋጅና አቅራቢ፡ ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከተባበሩት መንግስታት ኮቪድ-19 ምላሽ አሰጣጥ – ድጋፍ እና ፈንድ፣ ከተባበሩት መንግስታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት እና ከአይስአዲስ ጋር በመተባበር ትብብር 

የስልጠናው ዝርዝር፡ ዋና ዋና የቢዝነስ መርሆችን ካላወቅን አዲስ ቢዝነስ መስርተን ውጤታማ የመሆን እድላችን የጠበበ ነው። ይህ ሁሉም ውጤታማ አምራቾች(ስራ ፈጣሪዎች) ሊያውቋችው የሚገቡ ዋና ዋና የቢዝነስ መርሆች ለማስተማር በዘርፉ ሰፊ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች የተዘጋጀ የኢንተርኔት(online) ስልጠና ነው። ከህጋዊ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ጀምሮ እስከ ነባር ቢዝነስ ማሳደግ ዋና ጽንስ ሃሳቦችን የሚዳስስ ይሆናል። ስልጠናው የሚሰጠው በቴሌግራም በሚለቀቁ አምስት ቪድዮዎች ሲሆን በሚመቾት ጊዜ በማውረድ(download በማድረግ) ስልጠናውን መከታተል ይቻላል። ቪድዮዎቹ ለማውረድ እንዲመቹ በአነስተኛ ሚጋባይት ተደርገው የተቀናበሩ ናቸው። አምስት ምራፎችን የያዘው ስልጠና እያንዳንዳቸው አጫጭር ርዝማኔ (በአማካይ 15 ደቂቃ) ያላቸው ናቸው። ከያንዳንዳቸው የቪድዮ ትምህርቶች በተጨማሪ ተያያዥ የሆኑ አጋዥ የጽሁፍ ግባአቶች ለበለጠ እውቀት ለመስጠት አብረው ይለቀቃሉ። አምስቱ ምራፎች የሚከተሉት ናችው፡

ምዕራፍ አንድ : መግቢያ

ምዕራፍ ሁለት : ንግድ በኢትዮጵያ 

ምዕራፍ ሶስት :  የገበያ ጥናት አስተዳደር

ምዕራፍ አራት : የፋይናንስ አስተዳደር

ምዕራፍ አምስት : የንግድ ፍኖተ ካርታ

 ምዝገባ፡  የመመዝገብያ ቅጹን ”ይመዝገቡ”ን በመጫን ይህን አጭር የምዝገባ ቅጽ ሙሉ በሙሉ ከሞሉ በኋላ ማጠናቅቅያውን (submit) በመጫን የሚመልስሎትን የቴሌግራም ሊንክ በመጫና ግሩፑ ውስጥ በመቀላቀል ስልጠናውን ለመሳተፍ ይችላሉ።